እንግሊዝኛ የምዕራብ-ጀርመናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቋንቋ ነው። በዓለም ላይ በብዙ አገራት ውስጥ ይናገራል። የልደት ተናጋሪዎቹ ቁጥር 380 ሚሊዮን ያሕል ሲሆን በብዛት የምድር 3ኛ ቋንቋ ነው። ከዚህ በላይ እስከ 1 ቢሊዮን ሰዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይችሉታል።
እንግሊዝኛ በእንግሊዝ አገር ጀመረ። አንግል እና ሴያክስ የተባሉ ጀርመናዊ ጐሣዎች መጀመርያ የተናገሩት ጥንታዊ እንግሊዝኛ ይባላል። ነገር ግን ይህ እንደ ዛሬው እንግሊዝኛ በጣም አይመስልም። በ441 አ.ም. ጀምረው እነዚህ ጐሣዎች ከጀርመን ወጥተው በብሪታንያ ደሴት ሰፈሩ። ቋንቋቸውም የተጻፈበት "ሩን" በተባለው ጽሕፈት ነበር። በ7ኛ መቶ ዘመን ክርስትና ከተቀበሉ በኋላ ግን ቋንቋው በላቲን ፊደል ሊጻፍ ጀመረ።
ከ9ኛ መቶ ዘመን ጀምሮ ብዙ ሠራዊት ከዴንማርክና ከኖርዌ ወደ እንግሊዝ ስለ መጡ ተመሳሳይ ቋንቋ ስለነበራቸው ያን ጊዜ እንግሊዝኛ ከጥንታዊ ኖርስ አያሌ ቃሎች ተበደረ።
በ1058 ዓ.ም. ዊሊያም 1 "አሸናፊ" ከነሠራዊቱ እንግሊዝ አገርን ወርሮ ንጉስ ከሆነ በኋላ አዲስ መንግሥት ለማቆም ከፈረንሳይ መኳንንቶቹን ከሱ ጋራ አመጣ። የእንግሊዝ መንግሥት ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ለረጅም ጊዜ (300 አመቶች) እንግሊዝኛ ከትምህርት በቶች ተከለክሎ ቋንቋው ለጽሑፍ ሳይሆን እንደ መነጋገርያ ብቻ ስለ ቀረ በዚያን ጊዜ ብዙ ተለወጠ። እንግሊዝኛ በዚሁ ዘመን እጅግ ብዙ ቃላት ከፈረንሳይኛ ስለተበደረ በፍጹም ሌላ መልክ ይዞ አሁን መካከለኛ እንግሊዝኛ ይባላል። ቻውሰር አንድ ስመ ጥሩ የመካከለኛ እንግሊዝኛ ጸሐፊ ነበር።
በ15ኛ መቶ ዘመን "ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ" በሚባለው ለውጥ አናባቢዎቹ ተለውጠው የቋንቋው ድምጽ እንደገና ሌላ መልክ ያዘና ከዊሊያም ሼክፒር ዘመን ጀምሮ "ዘመናዊ እንግሊዝኛ" ተብሏል።
እንግሊዝኛ ከሌሎቹ ልሣናት ለምሳሌ ከቻይንኛ, ከህንዲ, ከጃፓንኛ እና ከእስፓንኛ አንዳንድ አዲስ ቃላት ከመውሰድ አላቋረጥም። ከተለያዩ አገሮች የነበሩት ሊቃውንት እርስ በርስ ለመነጋገር የቻሉ የጋራ ካወቁት ከሮማይስጥና ከግሪክ የጥናቶቻቸው ቃሎች በመምረጥ ነበር። እነዚያ የተክኖሎጂ ቃሎች ደግሞ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ፤ ለምሳሌ፣ photograph (ፎቶግራፍ) ከግሪክ photo- ፎቶ (ብርሀን) እና -graph ግራፍ (ሰዕል)፤ ወይም telephone (ተለፎን) ስልክ። ስለዚህ እንግሊዝኛ ከብዙ ቋንቋዎች ይሠራል።
Engels (taal) | Nīwu Englisc sprǣc | إنجليزية (لغة) | Inglés | Bahasa Inggris | Английски език | Ангельская мова | Saozneg | Anglès | Angličtina | Saesneg | Engelsk (sprog) | Englische Sprache | Inglise keel | Αγγλική γλώσσα | English language | Englische Sprache | Idioma inglés | Angla lingvo | زبان انگلیسی | Anglais | Béarla | Lingua inglesa | અંગ્રેજી ભાષા | 영어 | Անգլերեն | अंग्रेज़ी | Angla linguo | Pagsasao nga English | Lingua anglese | ᖃᓪᓗᓈᑎᑐᑦ | Enska | Lingua inglese | אנגלית | Basa Inggris | ინგლისური ენა | Sowsnek | Kiingereza | Lingua Anglica | Angļu valoda | Anglų kalba | Ingels | Angol nyelv | Англиски јазик | Anglisy fiteny | Bahasa Inggeris | Eng-gí | Inglestlahtoli | Bilagáana bizaad | Engels | Ingelsch | 英語 | Engelsk språk | Engelsk språk | Anglés | Āngalabhāsā | Język angielski | Língua inglesa | Limba engleză | Английский язык | Inglis leid | Eaŋgalsgiella | Engleski jezik | English language | Angličtina | Angleščina | Енглески језик | Englannin kieli | Engelska | Wikang Ingles | ஆங்கிலம் | ภาษาอังกฤษ | Tiếng Anh | Tok Inglis | İngilizce | Англійська мова | 英语