ኤንመርካር በሳንጋር (ሱመር) ነገስታት ዝርዝር ዘንድ ኡሩክ (ኦሬክ) ከተማ የመሰረተ ነበር፤ በዚያ ዝርዝር ጽህፈት 420 ዓመት እንደ ነገሰ ይላል። ደግሞ አባቱ የኡቱ ልጅ መስኪያግካሸር ወደ ባሕር ገብቶ ኤንመርካር መንግስቱን ከኤያና ከተማ እንዳመጣ ይጨምራል።
ኤንመርካር ካንዳንድ ሌሎች የሳንጋር አፈታሪክ ይታወቃል፤ በተለይም የሰው ልጅ ልሳናት መደባለቅ የሚናግር ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለው ተረት ራሱ የኡቱ ልጅ ይባላል። ኡቱ በሳንጋር እምነት የጸሓይ አምላክ ነበር። ኡሩክ ከመመስረቱ በላይ ታላቅ መስጊድ በኤሪዱ እንዳሰራ ይተረታል።
ዴቪድ ሮኅል የሚባል አንድ የታሪክ ሊቅ የኤንመርካርና የናምሩድ ተመሳሳይነት አመልክቷል። "-ካር" የሚለው ክፍለ-ቃል በሳንጋር ቋንቋ ማለት "አዳኝ" ሆኖ ኡሩክ የተመሠረተ በኤንመር-ካር ሲሆን፣ ደግሞ ናምሩድ፣ አዳኝ፣ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 10 ዘንድ ኦሬክን ሰራ። በብዙ አፈታሪኮች ደግሞ ናምሩድ የባቢሎን ግንብ መሪ የሆነ ነበር። በተጨማሪ ሮህል የኤሪዱ መጀመርያ ስም "ባቤል" እንደ ነበር ያስባል፤ እዚያም የሚገኘው የግንብ ፍረስራሽ የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ መሆኑን ገመተ።